የጦራ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

የጦራ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንጻ ዲዛይን

በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም የዕውቅና ሽልማት

በ2018 ዓመታዊ አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ፣ በዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

በ2018 ዓ.ም የላቀ አፈጻጸም የዕውቅና ሽልማት

በ2018 ዓመታዊ አፈጻጸም ከፍተኛና የላቀ ውጤት በማስመዝገብ፣ በዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የተበረከተ የዕውቅና ሽልማት።

የከተማችን ከፊል ገፅታ!

የሰላም የአብሮነት የፍቅር የአንድነት የመቻቻል መናገሻ የስልጤ ዞን ፈርጥ በፈጣን የእድገትና የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የምትገኘው የጦራ ከተማ አሰተዳደር

ፕሮጀክት ምልከታ

የመሰረት ልማት ፕሮጀክት ምልከታ

የአረንጓዴ አሻራ ጉዞ ስልማ 3

ጉዞ ስልማ 3 ጦራ - ላንፉሮ የክብር እንግዶች በመግባት ላይ

ፕሮጀክት ምልከታ

በስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ነይማ ሙኒር የተመራ ልዑክ በጦራ ከተማ አስተዳደር በመንግስትና በግል ባለሀብቶች እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ምልከታ አደረጉ!!

የ በርበሬ ምርትና መርታማነት

በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ ምርትና መርታማነት በርበሬ

የጦራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ደኑር ኮሪ መልዕክት

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃነት ውብ ተምሳሌት የሆነች ታላቅ ሀገር ናት። የተለያዩ ማንነቶች፣ እምነቶች፣ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች በአንድነት የደመቁባት ሀገራችን፣ ልዩነቷን ወደ ጥንካሬና ውበት በመቀየር ለዘመናት በመከባበርና በመቻቻል የኖረች ናት። ዜጎቿም ውድ ሕይወታቸውን በመስዋዕትነት በመክፈል የሀገራቸውን ሉዓላዊነትና ነፃነት አስከብረው ለትውልድ አስረክበዋል።

ነገር ግን ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የተፈጠሩ የተዛቡ ትረካዎችና የፖለቲካ አመለካከቶች ይህንን የጋራ እውነታችንን ለመሸርሸር ሞክረዋል። አንዳንድ ኃይሎችም አባቶቻችን የሀገር ምሰሶ ያደረጓቸውን እሴቶች የጥንካሬ ምንጭ ሳይሆን የድክመት ምንጭ ለማድረግ ሲሰሩ ቆይተዋል።የሀገራዊ ለውጡ ፈንጣቂ የሆነው የብልፅግና ፓርቲ ግን የሀገራችንን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በዘላቂነት መፈወስ የሚቻለው በአገራዊ አንድነት፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መንፈስ ውስጥ ብቻ እንደሆነ በፅኑ ያምናል። ለዚህም ነው አገራዊ አንድነታችንን በሕግ፣ በአሠራርና በተቋም ደረጃ የትኩረታችን ማዕከል ያደረግነው።

 በዚህ ታላቅ ጉዞ ውስጥ ጦራ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት በከተማዋ ነዋሪዎች የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል።ጦራ ከተማ የስልጤ ሕዝብ  የሰላም፣ የአንድነትና የልማት ማዕከል እንደመሆኗ፣ በተለያዩ ዘርፎች የሚመዘገቡ ውጤቶች የከተማዋን ብሎም የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የሚያበረክቱ ናቸው። ባለፉት ዓመታት ጦራ ከተማ የሰላምና የመረጋጋት አየር በማጠናከር፣ የከተማ ልማትን በማስፋፋት፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትን በማሳደግ እንዲሁም የሕዝብና የመንግስት ትስስርን በማጠናከር የሚታዩ ውጤቶችን አስመዝግበናል። የጦራ ከተማ የብልፅግና አሻራም በተጨባጭ እየጎላ መጥቷል። እርግጥ ነው፣ በጉዟችን ላይ ፈተናዎችና ተግዳሮቶች አጋጥመውናል። ሆኖም እኛ ፈተናዎችን ወደ መልካም አጋጣሚ፣ አቅማችንን ወደ ላቀ ውጤት፣ ተግዳሮቶችንም ወደ ታላቅ ስኬት በመቀየር፣ በመተሳሰብና በወንድማማችነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ውድ የሆነችውን ጦራ ከተማን፣ የስልጤን ሕዝብና ታላቋን ኢትዮጵያ ከፍ ለማድረግ በፅናት ወደፊት ተጉዘናል፤ ጉዟችንንም እንቀጥላለን! በጦራ ከተማ በየደረጃው የምትገኙ የፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መላው የከተማችን ማህበረሰብ፤ የውስጥ አንድነታችንን ይበልጥ በማጠናከር፣ ድህነትን፣ ስንፍናን፣ ሌብነትንና ሙስናን በቆራጥነት በመታገል፣ የድካማችን ማማና የልፋታችን ውጤት የሆነውን ሁሉን አቀፍ ብልፅግና ማረጋገጥ የምንችለው በጋራ ትጋትና በተቀናጀ ተሳትፎ ነው። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የጦራ ከተማ ነዋሪዎች እንደ ሁልጊዜው የጽናታችን አለኝታና የጉዟችን ደጋፊ ሆናችሁ ከጎናችን እንደምትቆሙ ሙሉ እምነት አለን። በመጨረሻም፣ ለዴሞክራሲያችን መጎልበት የማይተካ ሚና ያላችሁ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለጦራ ከተማ፣ ለስልጤ ሕዝብና ለታላቋ ኢትዮጵያ ብልፅግና ሲባል በትብብርና በጋራ እንድንቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ። 

                                                                                      ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት፣ ፍቅርና ልፋት ትበለፅጋለች!

                                                                                                            አመሰግናለሁ!"

አምልጦዎት ይሆን |You May Have Missed

     

ሚዲያ እና ገጽ| Our Media

አጋሮቻችን I Our Partner